አንድ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ 49 ጥያቄዎችና icon

አንድ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ 49 ጥያቄዎችና

4.0

A Muslim is the Qur'an and the kehādiši containing information relevant to blocking what should be the foundations of faith.

App Information

Version
Update
Mar 08, 2021
Developer
Installs
100,000+

App Names

App Description
አንድ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ 49 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው አብዛኛው የአንድ ሙስሊም የእምነት መሠረቶች ምን መሆን እንዳለባቸው የሚገልጽና ጥለቅ ማብራሪያ ከቁርዓን እና ከሐዲስ የያዘ ነው፡፡
የሚያካትተው ጥያቄዎችም
1. ሙስሊም እምነቱን ከየት ነው የሚወስደው?
2. በአንድ ነገር ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖርና ሳንግባባ ስንቀር ወደ ምን እንመለሳለን?
3. ከእሳት የሚድነው ቡድን የትኛው ቡድን ነው?
4. መልካም ተግባራትን አላህ ዘንድ ተቀባይ የሚያደርጉት መስፈርቶች ስንት ናቸው?
5. የእስልምና ሃይማኖት ደረጃዎች ስንት ናቸው?
6. ኢስላም ምንድነው? ማዕዘናቱስ ስንት ናቸው?
7. ኢማን ምን ማለት ነው?
8. የላኢላህ ኢለሏህ ትርጉም ምንድን ነው?
9. አላህ ከኛ ጋር ነውን?
10. አላህ በአይን ይታያልን?
11. የአላህን ስሞችና ባህሪያቶች ማውቅ ጥቅሙ ምንድን ነዉ?
12. በአላህ ስሞችና ባህሪያቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
13. በመላኢኮች ማመን ማለት ምን ማለት ነው?
14. ቁርዓን ምንድን ነው?
15. ሀዲሰን ትተን በቁርዓን ብቻ መብቃቃት ይቻላልን?
16. በነብያት ማመን ምን ማለት ነው?
17. በቂያማ ቀን የሚኖሩት የሸፈዓ(ሽምግልና) ወይም ምልጃ አይነቶች ስንት ናቸው?
18. በህይወት ካሉ ሰዎች እገዛንም ሆነ ሽምግልናን መጠየቅ ይቻላልን?
19. ተወሱል(ወደ አላህ መቃረብ መጠጋት) ስንት ክፍል አለው?
20. በመጨረሻ ቀን ማመን ምን ማለት ነው?
21. የቂያማ ታላላቅ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
22. በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የምታልፈው ታላቋ ፈተና የትኛዋ ናት?
23. በአሁኑ ሰዓት ጀነትና እሳት ተፈጥረው ይገኛሉን?
24. በቀደር ማመን ማለት ምን ማለት ነው?
25. ፍጡር ነገሮችን በራሱ የመምረጥ ፍላጎት አለውን?
26. ኢህሳን ማለት ምን ማለት ነው?
27. የተውሂድ ክፍሎች ስንት ናቸው?
28. ወሊይ ማንነው?
29. ስለ ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ባለድረቦች ያለብን ግዴታ ምንድነው?
30. ነቢዩ ሙሐመድን(ሰ.ዐ.ወ) ከተሰጡት ደረጃ በላይ በሙገሳ ማጋነን ይፈቀዳልን?
31. እውነት የመፅሐፍ ሰዎች አማኞች ይባላሉን?
32. ከሃዲዎችን ያለምንም ጥፋት መበደል ይፈቀዳልን?
33. ቢድዕ ምንድን ነው?
34. ቢድዕ በኢስላም መልካምና መጥፎ ተብሎ ለሁለት ይከፈላልን?
35. የንፍቅና አይነቶች ስንት ናቸው?
36. አላህ ዘንድ ትልቁ ወንጀል(ሀጢአት) ምንድን ነው?
37. የማጋራት አይነቶች ስንት ናቸው?
38. . በትልቁ ሽርክ(ማጋራት) እና በትሹ መሃከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
39. ሽርክ ሳይከሰት በፊት መከላከያቸው ምንድን ነው?
40. በአላህ መካድ ሲባል ስንት አይነት ነው?
41. በኢስላም ስለት መሳል እንዴት ይታያል?
42. ወደ ጠንቋይ ወይም አውቃለሁኝ ባይ ዘንድ መሔድ ኢስላማዊ ብያኔው ምንድነው?
43. ዝናብን በኮከብ መለመን እንደ ማጋራት የሚሆነው መቼ ነው?
44. ለሙስሊም መሪዎች ያለብን ግዴታ ምንድን ነው?
45. አላህ ‹‹ ከመልካም ነገር የሚያገኝህ ከአላህ ችሮታ ነው፡፡ ከመከራም የሚደርስብህ ከራስ (ጥፋት የተነሳ ነው) ማለቱ ምን ማለት ነው?
46. እገሌ ሰመዕት (ሸሂድ) ነው ወይም ሸሂድ ሆነ ማለት ይፈቀዳል?
47. አንድን ሙስሊም የሆነን ሰው ለይቶ ከሃዲ ነው ማለት ይቻላል?
48. .ጦዋፍን ከካዕባ በቀር በሌላ ቦታ ማድረግ ይቻላልን?
ለሚሉት ጥያቄዎች ጥለቅ ማብራሪያ ከ ሐዲስና ቁርዓን የያዘ ነው፡፡
Read more